Esubalew Mulat

«በቅተሽ እይው»

ይላሉ የምወዳቸው።

ለሰማዩም ለምድሩም፣ ለትንሹም ለትልቁም የሚሆን የምልከታ የሃሳብ አምኀ ነው።


Profile Pic

Professional Profile

A dedicated academic and technical expert focused on innovation, research, and fostering growth in technology and human capabilities.

Academic & Tech

Greetings,

My name is Esubalew. I'm a computer engineer and a lecturer at Addis Ababa Science and Technology University.

Professionally, I am dedicated to advancing knowledge and technology. In life, I am an advocate of humanity, real wisdom, and metaphysical values. I am passionate about building solutions that solve practical existing problems, and I have hands-on experience in Mobile Application and Web Development with a growing research focus on the blend of AI and IoT, AIoT.

"My prime desire in life is to make every moment, down to the smallest fraction of time, truly count."

— Esubalew Mulat

ከአክብሮት ጋራ ሰላም !

ማን ነህ ቢሉ ብዙ ማንነት ያለውን የሰው ልጅ በቀላሉ እንዲህ ነው አይሉም። አቅልለን ወይንም በሆነ ልክ ወስነን ግን እንዲህም እንዲያም ነው እንላለን። እናም እላለሁ፦ እኔ የኮምፒዩተር ምህንድስና ባለሙያ፣ መምህር፣ ከሕይወት መማር የምፈልግ የሕይወት ዘመን ተማሪ ነኝ እላለሁ። በጎ ስብዕናን፣ እውቀትንና ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ይጠቅማል ይገባልም እላለሁ። ስሜም እሱባለው ይባላል።

በአእምሮህ ውስጥ ያለ አንድ ነገር ተናገር ብባል፦"ነገ ላይ እንደማይሳካ በትክክል የተረዳሁት ጉዳይ ቢኖር ተስፋ ለመቁረጥ ነገን አልጠብቅም" እላለሁ። ይህ ጉዳይ ስለተስፋ መቁረጥ ግን አይደለም። ለተግባርና ከአንደበትና ከድስኩር (Propaganda) በላይ ሆኖ መሬት ላይ ላለ ሐቅ ልዩ ቦታ ስላለኝ እንጅ። ሞባይል መተግበሪያ and የድረ ገጽ ልማት wከፍተኛ ከሆነ የንጹሕና የተግባራዊ ምርምር ክህሎት AIoT.

"ነገ ላይ እንደማይሳካ በትክክል የተረዳሁት ጉዳይ ቢኖር ተስፋ ለመቁረጥ ነገን አልጠብቅም "

— እሱባለው

Roles & Expertise

  • Lecturer
  • Computer Engineer
  • Researcher

Core Technical Areas:

Artificial Intelligence Internet of Things (IoT) Cyber Security

Principles & Virtues

Understanding, Compassion, Calmness, Wisdom
Intuition, Faith, Spirituality, Cosmic Consciousness, Incorruptible Truth

Priority: ፩..፫..፫

  • • Love
  • • Patience
  • • Humility

Philosophy & Outcomes

Wonder.

Triumph.

Fragrance.

Peace.

Eternity.

  • System | Institution
  • Design | Risk Mgmt
  • Discernment over the pile
  • Action | Small Steps

Why this Website?

  • This is my main preffered point of contact for my academic, business, and personal pursuits.
  • I'll share thoughts, reflections and observations that I find worth to share.
  • It is a place for sharing academic contents for public use.
  • Provide articles and book reviews of my own or others.
  • Also, for certain professional and technical purposes not detailed here.

እንዲህ አስባለሁ

ድንገት የሚባል ነገር የለም ባልልም



ብዙ ጊዜ ያልተጠኑና በድንገቴ ብቻ ጊዜ የሚወልዳቸው ነገሮች የሉም። በሚታይም በማይታይም መልኩም ቢሆን ነገሮች የሚሄዱት አስቀድሞ በተጠና ትልም መሠረትነት [ አንድም አስቀድሞ ባለ ደግም ክፉም ምኞትና ፍላጎት] ነው። የዓለም ብዙ ምስቅልቅሎች አስቀድመው የታቀደባቸው፣ ንድፍ የወጣላቸው (designed)፣ ማስፈጸሚያ ሥርዓትና መዋቅር (system and structure) የተዘጋጀላቸው ናቸው። በሥርዓት የመጣን ሁነት በእርግማን፣ በስሜትና በመሰለኝ ለማስወገድ መሞከር በእኔ ፊት ሞኝነት ነው።

ነገረ ሳይንስ



ሳይንስ ጥበብ ነው፤ ሃብት ነው፤ ታላቅ ነገርም ነው። ሳይንስ ድንቅ፣ ልዩና እልቆ ቢስ የሆነውን ሥነ ተፈጥሮም ሆነ ሥነ መለኮት በመግለጥ ረገድ ግን ድንክ ነው። ሳይንስን ለበጎነት ከመጠቀም አልፎ ያለልክ በሳይንስ የሚደገፍ አንድም እምነቴ ሳይንስ ነው የሚል ሰው ግን እጅግ ያሳዝነኛል። ሳይንሳዊ የሆኑ መስሏቸው ሳይንስ "ሀ" ብሎ የሚጀምርበትን መነሻ መሠረት ወዳለማስተዋል እንደሄዱ እንኳ የማይገነዘቡ አሉ። ጤናማ ሳይንስ ታላቅ ዋጋው እንዳለ ሆኖ ትህትና፣ ማስተዋልና ጥበብ ባልተለየው እምነት የሚኖር ሰው ቢኖር ግን የማይጨበጥና የሌለ የሚመስለውን ዓለም ወደማስተዋል፣ ወደማመን፣ ወደመረዳት፣ ወደማወቅና ከዚህም ባለፈ ገና ምድር ላይ እያለ ጥርጥር በሌለበት ፍጹም እርግጠኝነት በመኖር በዓይን ላይ ዓይን፣ በእጅ ላይ እጅ፣ በእውቀት ላይ ጥበብ፣ በጥበብ ላይ ድንቅን ይጨምራል።

የማያቋርጥ እድገት



ሰው ሊረዳ የሚችለው በደረሰበት ደረጃ ልክ ብቻ ነው። በደንብ የሰለጠነባቸውና ከደረጃው በታች ያሉ ነገሮች ቢኖሩ የተዋሃዱት እስኪመስሉ ድረስ ደርሶ አጥርቶ፣ አስፍቶና አራቆ ይረዳቸዋል። በልኩ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮች ቢኖሩ እየተገነዘበ ይመረምራቸዋል፣ ደስ ይሰኝባቸዋል። በደንብ ጭብጥ ባያደርጋቸውም ደርሶባቸው ይነካካቸዋል። ከእሱ ደረጃ ጥቂት ከፍ ያሉ ነገሮች ቢነገሩት ደግሞ ይደመምባቸዋል፣ ይናፍቃቸዋል፣ ያደንቃቸዋል። ከእሱ ደረጃ እጅግ ከፍ ያሉ ነገሮች ቢኖሩ ግን ፈጽሞ ሊረዳቸው አይችልም፣ አይገቡትም፣ ተረት ተረትና ሞኝነትም ይመስሉታል። አለፍ ሲልም አይወዳቸውም፣ ይንቃቸዋል፣ ይሰድባቸዋል፣ ያሽካካባቸዋልም። ብዙ ጊዜ ድንቅ ሚስጥሮች፣ የረቀቁ ደረቅ እውነቶች፣ አንድም መዓዛ ሕይወቶች አንድም ራሳቸው ሕይወት የሆኑት ሁሉ የሚረገጡበት ምክንያት ይህ ነው። ለዚህም ነው ሰው በማያቋርጥ እድገት ውስጥ ሊኖር የተገባው።

ይበልጥ የሚያስፈልገን በምልዓት ያለው ነው



ለሕይወት የግድ የሆኑ ነገሮች በመጠን መብዛታቸው፣ በብዛታቸው ልክ ግን ዋጋቸው የተናቀ መሆኑን ሳስብ ይገርመኛል። ረብ ለሌላቸው ነገሮች ብዙ ሰው ሲራወጥ ይታያል። ከዚህም አልፎ ለእነዚህ ለሕይወት የረባ ጥቅም ለሌላቸው ጉዳዮች ውድ ሕይወት ይነጠቅበታልም። አምስት ስድስት ቀን ውሃ የሌለበት እጅግ ጥቂት ደረቅ ቂጣ ብቻ ብላ ቢባል የውሃን ዋጋ ሌላ ምንም ነገር እስከማያስደስተው ድረስ ደርሶ በአምስት ቀን ብቻ በሚገባ ያውቀዋል። ለደቂቃ አየር እንዳይወስድ የታፈነ ወይንም በ Oxygen Therapy ሕይወቱን የሚያስቀጥል ቢኖር በምልዓት በዝቶና ለብዙኀኑ ዋጋ ቢስ መስሎ የሚታየው የአየር - የኦክስጅን ዋጋ ምንነት ይገባዋል። በውድ ከምንገዛቸው ከብዙ ነገሮች ይልቅ ውሃ በብዛት ይገኛል፤ አብዝቶ ግን ያስፈልገናል። ከውሃ ይልቅ አየር በብዛት ይገኛል የበለጠ ግን ያስፈልገናል። ከአየርም ሆነ ከውሃ ይልቅ ግን ምሕረተ እግዚአብሔርና ፍቅረ እግዚአብሔር አንድም የእርሱ ጥበቃ ያለወሰን በምልዓት መልቶ ይኖራል። ምሉዕ ነውና ዋጋው አይገባንም።

ጊዜ መግዛት



ማን ያሸንፋል ቢሉኝ በምን ጉዳይ የሚለውን ልተወውና ጊዜን መግዛት የቻለ እላለሁ። በቃ ጊዜን መግዛት የቻለ እሱ አሸናፊ ነው።.

             
        
  
        

Quotes in my Mind

Does simple or common mean less important? No. That is why I'm impressed with the following.

"Educating the mind without changing the heart is no education at all!"

Aristotle

Greek Philosopher

"We do not inherit the earth from our ancestors, we borrow it from our children."

Unknown Source

- OR I don't know it yet -

"The worst form of inequality is to try to make unequal things equal."

Aristotle

Greek Philosopher

"Common sense is a collection of prejudices acquired by age 18."

Alber Einstein

Scientist